Popular posts from this blog
በጣና ሃይቅ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ የሞቱት ሰዎች 12 ደረሰ
በጣና ሃይቅ በደረሰ የጀልባ መገልበጥ አደጋ የሞቱት ሰዎች ቁጥር 12 ደረሰ:: ጀልባዋ ከባህር ዳር ዙሪያ ወረዳ ሰቀለጥ ከተባለ ቦታ ወደ ደቅ ደሴት ዘጠኝ መንገደኞችን አሳፍራ ስትጓዝ እንደነበረ ከጣና ሃይቅ ትራንስፖርት ድርጅት የተገኘነው መረጃ ያመላክታል። በአደጋው ሳቢያም የዘጠኝ ሰዎች ህይዎት ማለፉን ድርጅቱ ገልጿል። እስካሁን የአንድ ሰው አስከሬን የተገኘ ሲሆን፥ የቀሪ ስምንት ሰዎችን አስከሬን የማፈላለጉ ስራ እየተሰራ ነው ተብሏል። የአደጋውን መንስኤ የሚያጣራ መርማሪ ቡድን ወደ ስፍራው መላኩንም ድርጅቱ አስታውቋል። አደጋው ትናት ንጋት 11፡00 ላይ ሳይደርስ እንዳልቀረም ከአማራ ብዙሃን መገናኛ ድርጅት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አዲስ አበባ ፣ ታህሳስ 22 ፣ 2011 (ኤፍ ቢ ሲ)
ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ ክለቦች የልምምድ እና ስቴዲየም መስሪያ ቦታ ሊሰጥ ነው
የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ለኢትዮጵያ ቡና እና ቅዱስ ጊዮርጊስ የእግር ኳስ ክለቦች የልምምድ እና ስቴዲየም መስሪያ ቦታ ሊሰጥ መሆኑን አስታወቀ። የስፖርት ክለቦቹ በተደጋጋሚ የልምምድ መስሪያ ቦታ እና የማስፋፊያ ቦታ ችግር እንዳለባቸው በተለያየ ጊዜ ለከተማ አስተዳደሩ ጥያቄዎችን ሲያቀርቡ ቆይተዋል። ስለሆነም አዲሱ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ጥያቄው አግባብነት ያለው መሆኑን በመገንዘብ ለሁለቱም የከተማችን ክለቦች የልምምድ መስሪያ ቦታ ለመስጠት ውሳኔ ላይ መድረሱ ነው የተገለፀው። ከዚህ ባለፈም መስተዳድሩ የስፖርት ክለቦቹ እራሳቸውን ለማሳደግ በሚያደርጉት ጥረት ላይ አስፈላጊውን ድጋፍ ለማድረግ ዝግጁ መሆኑን ከከንቲባ ፅህፈት ቤት ያገኘነው መረጃ ያመላክታል። አዲስ አበባ ፣ታህሳስ 21፣2011 (ኤፍ ቢ ሲ) https://fanabc.com

oduu gaariidha
ReplyDelete